Welcome to Addis Ababa City Food and Drug Administration and Authority Kirkos Branch Cluster 1 Office!       እንኳን ወደ አዲስ አበባ ከተማ ምግብና መድኃኒትና ባለስልጣን ቂርቆስ ቅርንጫፍ ክላስተር 1 ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና ሳይንስን መሠረት ያደረገ የምግብ፣ መድሃኒት፣ ጤና እና ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ስራ ተዘርግቶ ነዋሪዎቿ የቁጥጥሩ ባለቤት የሆኑበትና ጤናማ ማህበረሰብ የሚኖርባት ከተማ ሆና ለማየት ይተጋል!
image
image
image
image
image

በአዲስ አበባ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ቂርቆስ ቅርጫፍ ክላስተር 1ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት የ6ወር ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ እና በአዋጅና ደንብ እንዲሁም በመመሪያ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ::

ጥር 8, 2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብ መድሃኒት ባለስልጣን ቂርቆስ ቅርንጫፍ ክላስተር 1 የ2018 በጀት ዓመት የ6ወር አፈጻጸም እና በአዋጅና ደንብ እንዲሁም በመመሪያ ከጤና ፎረም፣ ከባለድርሻ አካላት፣ ከንግዱ ማህበረሰብና ከነዋሪው ጋር ዉይይት አካሄደ። የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ክላስተር 1 ጽ/ቤት ባለሙያ ወ/ሮ ሀና አስማረ ቂርቆስ ክላስተር 1 ወረዳ1 ፣7እና 8 ትን ያቀፈ ነው በማለት ባለፉት ስድስት ወራት ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ በርካታ ስራዎች መሰራተቸውን በመግለጽ በጽ/ቤቱ የህብረተሰብ ጤና እና ደህንነት ለማስጠበቅ በመደበኛ ቁጥጥር እንዲሁም በዘመቻ በርካታ ስራዎች መከናወናቸዉን ጠቅሰዉ በእቅድ ከተያዙት ስራዎች በተጨማሪ ሌብነትና ብልሹ አሰራር ከመከላከል አንጻር፣ተቋማዊ ውጤታማነት በማሻሻል የሰራተኛና ተገልጋይ እርካታ ከማሳደግ አንጻር፣ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠርና አገልግሎትን ከማሻሻል አንጻር እንዲሁም የህዝብ፣ሲቪል ማኅበራትና የግል ሴክተር ተሳትፎ ስርዓትን ከማሳደግ አንፃር በ6 ወራት ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል። ‎ ባለሙያዋ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት በክላስተር ጽ/ቤቱ በወረዳው ለሚገኙ የምግብ መሸጫ እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ እንዲሁም ጤናነክ አገልግሎትና የምግብ አምራች ተቋማት ላይ ቁጥጥር በማድረግ ደረጃውን ለሚያሟሉ ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ እድሳት እና አዲስ የብቃት ማረጋገጫ ሲሰጥ እንደነበር ገልፀው ከተቋማትና ከግለሰቦች የሚመጡ ቅሬታና አቤቱታዎችን በመቀበል በርካታ ተግባራቶችን ማከናወናቸው አብራርተዋል:: በ6ወሩም ከተቋማት 48.ሺ ብር ገቢ እንደተሰበሰበም በሪፓርቱ ላይ ገልጸዋል:: በሌላ በኩል የክላስተር 1 ፅ/ቤት ቡድን መሪ ሚስጥረ ዮሐንስ በትምባሆ እና አደንዛዥ እፅ ጋር በተያያዘ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በዚህም ጤናማ ፣በስነ ምግባር የታነፀ ዜጋ እንዲኖርና ንፁህ አካባቢ ለመፍጠር ማጨስ በህግ የተከለከለ መሆኑን ሁሉም በማወቅ ግንዛቤ መያዝ አለበት ብለዋል:: ‎ በመጨረሻም ባለድርሻ አካላቱ የማህበረሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ከቤቱም ለቀረቡ ሀሳቦች፣ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የክላስተር1 የጽ/ቤቱ ቡድን መሪና ባለሙያ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን አንዳንድ ቀሪ ስራዎች ያሉ መሆናቸውን በመግለጽ የባለድርሻ አካላቱ ተሳትፎና ሚና ወሳኝ መሆኑን ገለጸው በቀጣይነት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ አቅጣጫ በማስቀመጥ የጥቆማ ነጻ 8864 ላይ ጥቆማ በመስጠት እንደሚቻል በመግለጽ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ መድረኩ ተጠናቋል:: ‎

መልዕክትዎን ይላኩ