Welcome to Addis Ababa City Food and Drug Administration and Authority Kirkos Branch Cluster 1 Office!       እንኳን ወደ አዲስ አበባ ከተማ ምግብና መድኃኒትና ባለስልጣን ቂርቆስ ቅርንጫፍ ክላስተር 1 ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና ሳይንስን መሠረት ያደረገ የምግብ፣ መድሃኒት፣ ጤና እና ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ስራ ተዘርግቶ ነዋሪዎቿ የቁጥጥሩ ባለቤት የሆኑበትና ጤናማ ማህበረሰብ የሚኖርባት ከተማ ሆና ለማየት ይተጋል!
image
image
image
image
image

የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ መሆኗን ተከትሎ ለ39ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ ለሚመጡ እንግዶች ማረፊያ በሆኑ በተመረጡ 30 ሆቴሎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ጀምሯል።

ጥር 21, 2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ለ39ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ወደ አገራችን ለሚመጡ እንግዶች የሚያገለግሉ ሆቴሎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እንደመሆኗ በየዓመቱ ከፍተኛ የአፍሪካ እና የዓለም አቀፍ መሪዎችን በመቀበል ረገድ ልዩ ኃላፊነት እንዳለባት ይታወቃል፣ አንደባለስልጣን መስሪያ ቤት ይህ ቁጥጥርም የአገሪቱን መልካም ገጽታ ለማስጠበቅ እንደሚረዳም ተጠቁሟል። ቁጥጥሩ ባለአራትና ባለአምስት ኮከብ ሆቴሎችን ጨምሮ ለጉባኤው የተመረጡ 30 ሆቴሎችን የሚያካትት ሲሆን፣ በተለይም የመኝታ ክፍሎች፣ የምግብ ማብሰያ ቦታዎች እና የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቶች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራበት ይገኛል። በቁጥጥሩ ወቅት የሚገኙ ክፍተቶች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት የማስተካከያ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ባለስልጣኑ ገልጿል። በተለይም ሁሉም በከተማችን ያሉ ሆቴሎች በአገራችን ባህልና ወግ መሰረት ለእንግዶች ቅድሚያ ለመስጠት በሚያስችል አግባብ የተሟላ ዝግጅት እንዲያደርጉ ከወትሮ የተለየ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ እንደሆነም ተገልጿል ። ቁጥጥሩ ጉባኤው እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚቀጥል ሲሆን፣ ዓላማው ሊከሰቱ ከሚችሉ ተላላፊ በሽታዎች እንግዶችን መከላከልና ኢትዮጵያን እንደ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማዕከል ያላትን ሚና ማጠናከር መሆኑ ተገልጿል።

መልዕክትዎን ይላኩ