Welcome to Addis Ababa City Food and Drug Administration and Authority Kirkos Branch Cluster 1 Office!       እንኳን ወደ አዲስ አበባ ከተማ ምግብና መድኃኒትና ባለስልጣን ቂርቆስ ቅርንጫፍ ክላስተር 1 ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና ሳይንስን መሠረት ያደረገ የምግብ፣ መድሃኒት፣ ጤና እና ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ስራ ተዘርግቶ ነዋሪዎቿ የቁጥጥሩ ባለቤት የሆኑበትና ጤናማ ማህበረሰብ የሚኖርባት ከተማ ሆና ለማየት ይተጋል!
image
image
image
image
image

የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ስጋት ተኮር በሆኑ የቁጥጥር ስራዎች እና የባለሙያ ስነመግባር ላይ በቀጣይ ስለሚሰሩ ስራዎች ውይይት ተካሄደ።

የካቲት 2, 2018
የምግብና ጤና ነክ ቁጥጥር ዳሬክቶሬት የህዝብ ጤናን ለመጠበቅ እና የምግብ ደህንነትን ለማረጋገጥ በሚያከናውናቸው የቁጥጥርና ክትትል ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ የውይይት መድረክ ከቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች የዘርፉ ዳሬክተሮችና የቡድን መሪዎች ጋር ውይይት አካሂዷል። መድረኩ የተካሄደበት ዋና ዓላማ በተከናወኑ የቁጥጥር ስራዎች ላይ የተገኙ ውጤቶችን በመገምገም፣ የተለዩ ክፍተቶችን መለየት እና በቀጣይ የሚሰሩ የስራ አቅጣጫዎችን በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር የጋራ መግባባት መፍጠር መሆኑ ተገልጿል። ለውይይቱ መነሻ በስጋ ቤቶች ላይ የተከናወኑ የቁጥጥር ስራዎች፣ በትምህርት ቤቶች ምገባ ላይ በሀይጅንና ሳኒቴሽን ዙሪያ የተደረጉ ክትትሎች፣ በትንባሆ ምርትና ንግድ ላይ የተካሄዱ የቁጥጥር ስራዎች እንዲሁም በዘይት አምራች ተቋማት ላይ የተሰሩ ስራዎች በዝርዝር ቀርበዋል። በመድረኩ የባለስልጣኑ የቁጥጥር ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ እንጋ እርቀታ ተገኝተው ንግግር ሲያደርጉ፣ ተቋሙ በቀጣይ የሚያተኩራቸውን ዋና ዋና የስራ አቅጣጫዎች አስቀምጠዋል። አቶ እንጋ እንደገለጹት፣ ስጋት ተኮር ቁጥጥርን ማጠናከር፣ ተቋማት ራሳቸውን እንዲቆጣጠሩ ማስቻል፣ ድንገተኛ ቁጥጥሮችን አጠናክሮ መቀጠል፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን ማስፋት እና የቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር የተቋሙ ዋና የቀጣይ አቅጣጫዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም አዋጅ፣ ደንብና መመሪያዎችን በሚጥሱ እና ለህዝብ ጤና ስጋት በሚያመጡ ተቋማት ላይ ተገቢ እርምጃ መውሰድ የማይታለፍ መሆኑን በንግግራቸው አጽንኦት ሰጥተዋል። ውይይቱ የጋራ መግባባትን በማጠናከር የቁጥጥር ስራዎች በተቀናጀና በውጤታማ መልኩ እንዲፈጽሙ አጋዥ መሆኑ በተሳታፊዎች ተገጿል።

መልዕክትዎን ይላኩ