Welcome to Addis Ababa City Food and Drug Administration and Authority Kirkos Branch Cluster 1 Office!
እንኳን ወደ አዲስ አበባ ከተማ ምግብና መድኃኒትና ባለስልጣን ቂርቆስ ቅርንጫፍ ክላስተር 1 ጽ/ቤት በሰላም መጡ!
ጽ/ቤቱ አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና ሳይንስን መሠረት ያደረገ የምግብ፣ መድሃኒት፣ ጤና እና ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ስራ ተዘርግቶ ነዋሪዎቿ የቁጥጥሩ ባለቤት የሆኑበትና ጤናማ ማህበረሰብ የሚኖርባት ከተማ ሆና ለማየት ይተጋል!
ለገሀር የሃ ሲቲ ሴንተር 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 30
+251955261273
የቅሬታ አስተያየት መስጫ
ዓርብ, ህዳር 14, 2016 ዓ.ም
መግቢያ
ስለ እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የዜጎች ስምምነት ሰነድ
ተቋማዊ አደረጃጀት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች
የደንበኞች አገልግሎት
ዋና ዋና አገልግሎቶች
የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች ቁጥጥር ቡድን ስራዎች
የአገልግሎት እርካታ አስተያየት መስጫ
የቅሬታ አስተያየት መስጫ
ለመልካም አስተዳደር አስተያየት
የጽ/ቤቱን ሮቦት ይጠይቁ
ሚዲያ
ዜና | News
Online TV
መጽሄቶች | Magazines
ጠቃሚ መረጃዎች
ደንብና መመሪያዎች
የዶ/ር ዐቢይ መጽሀፍቶች
ብሮሸር | Brochure
በራሪ ወረቀት
ማስታወቂያ
ይግቡ
መግቢያ
ስለ እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
የዜጎች የስምምነት ሰነድ
አገልግሎቶች
ተቋማዊ አደረጃጀት
ሚዲያ
ዜናዎች | News
መጽሄቶች | Magazine
Online TV
ጠቃሚ መረጃዎች
ደንብና መመሪያዎች
ብሮሸር
የደንበኞች የእርካታ ዳሰሳ ገጽ
Web APP
ወረዳዎች
ወረዳ 1
ወረዳ 2
ወረዳ 3
ወረዳ 4
ወረዳ 5
ወረዳ 6
ወረዳ 7
ወረዳ 8
ወረዳ 9
ወረዳ 10
ይግቡ
ዜና | Oduu | News
በአዲስ አበባ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ቂርቆስ ቅርጫፍ ክላስተር 1ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት የ6ወር ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ እና በአዋጅና ደንብ እንዲሁም በመመሪያ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ::
ጥር 8, 2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብ መድሃኒት ባለስልጣን ቂርቆስ ቅርንጫፍ ክላስተር 1 የ2018 በጀት ዓመት የ6ወር አፈጻጸም እና በአዋጅና ደንብ እንዲሁም በመመሪያ ከጤና ፎረም፣ ከባለድርሻ አካላት፣ ከንግዱ ማህበረሰብና ከነዋሪው ጋር ዉይይት አካሄደ። የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ክላስተር 1 ጽ/ቤት ባለሙያ ወ/ሮ ሀና አስማረ ቂርቆስ ክላስተር 1 ወረዳ1 ፣7እና 8 ትን ያቀፈ ነው በማለት ባለፉት ስድስት ወራት ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ በርካታ ስራዎች መሰራተቸውን በመግለጽ በጽ/ቤቱ የህብረተሰብ ጤና እና ደህንነት ለማስጠበቅ በመደበኛ ቁጥጥር እንዲሁም በዘመቻ በርካታ ስራዎች መከናወናቸዉን ጠቅሰዉ በእቅድ ከተያዙት ስራዎች በተጨማሪ ሌብነትና ብልሹ አሰራር ከመከላከል አንጻር፣ተቋማዊ ውጤታማነት በማሻሻል የሰራተኛና ተገልጋይ እርካታ ከማሳደግ አንጻር፣ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠርና አገልግሎትን ከማሻሻል አንጻር እንዲሁም የህዝብ፣ሲቪል ማኅበራትና የግል ሴክተር ተሳትፎ ስርዓትን ከማሳደግ አንፃር በ6 ወራት ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል። ባለሙያዋ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት በክላስተር ጽ/ቤቱ በወረዳው ለሚገኙ የምግብ መሸጫ እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ እንዲሁም ጤናነክ አገልግሎትና የምግብ አምራች ተቋማት ላይ ቁጥጥር በማድረግ ደረጃውን ለሚያሟሉ ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ እድሳት እና አዲስ የብቃት ማረጋገጫ ሲሰጥ እንደነበር ገልፀው ከተቋማትና ከግለሰቦች የሚመጡ ቅሬታና አቤቱታዎችን በመቀበል በርካታ ተግባራቶችን ማከናወናቸው አብራርተዋል:: በ6ወሩም ከተቋማት 48.ሺ ብር ገቢ እንደተሰበሰበም በሪፓርቱ ላይ ገልጸዋል:: በሌላ በኩል የክላስተር 1 ፅ/ቤት ቡድን መሪ ሚስጥረ ዮሐንስ በትምባሆ እና አደንዛዥ እፅ ጋር በተያያዘ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በዚህም ጤናማ ፣በስነ ምግባር የታነፀ ዜጋ እንዲኖርና ንፁህ አካባቢ ለመፍጠር ማጨስ በህግ የተከለከለ መሆኑን ሁሉም በማወቅ ግንዛቤ መያዝ አለበት ብለዋል:: በመጨረሻም ባለድርሻ አካላቱ የማህበረሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ከቤቱም ለቀረቡ ሀሳቦች፣ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የክላስተር1 የጽ/ቤቱ ቡድን መሪና ባለሙያ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን አንዳንድ ቀሪ ስራዎች ያሉ መሆናቸውን በመግለጽ የባለድርሻ አካላቱ ተሳትፎና ሚና ወሳኝ መሆኑን ገለጸው በቀጣይነት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ አቅጣጫ በማስቀመጥ የጥቆማ ነጻ 8864 ላይ ጥቆማ በመስጠት እንደሚቻል በመግለጽ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ መድረኩ ተጠናቋል::
ዜና | Oduu | News
የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ስጋት ተኮር በሆኑ የቁጥጥር ስራዎች እና የባለሙያ ስነመግባር ላይ በቀጣይ ስለሚሰሩ ስራዎች ውይይት ተካሄደ።
የካቲት 2, 2018
የምግብና ጤና ነክ ቁጥጥር ዳሬክቶሬት የህዝብ ጤናን ለመጠበቅ እና የምግብ ደህንነትን ለማረጋገጥ በሚያከናውናቸው የቁጥጥርና ክትትል ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ የውይይት መድረክ ከቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች የዘርፉ ዳሬክተሮችና የቡድን መሪዎች ጋር ውይይት አካሂዷል። መድረኩ የተካሄደበት ዋና ዓላማ በተከናወኑ የቁጥጥር ስራዎች ላይ የተገኙ ውጤቶችን በመገምገም፣ የተለዩ ክፍተቶችን መለየት እና በቀጣይ የሚሰሩ የስራ አቅጣጫዎችን በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር የጋራ መግባባት መፍጠር መሆኑ ተገልጿል። ለውይይቱ መነሻ በስጋ ቤቶች ላይ የተከናወኑ የቁጥጥር ስራዎች፣ በትምህርት ቤቶች ምገባ ላይ በሀይጅንና ሳኒቴሽን ዙሪያ የተደረጉ ክትትሎች፣ በትንባሆ ምርትና ንግድ ላይ የተካሄዱ የቁጥጥር ስራዎች እንዲሁም በዘይት አምራች ተቋማት ላይ የተሰሩ ስራዎች በዝርዝር ቀርበዋል። በመድረኩ የባለስልጣኑ የቁጥጥር ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ እንጋ እርቀታ ተገኝተው ንግግር ሲያደርጉ፣ ተቋሙ በቀጣይ የሚያተኩራቸውን ዋና ዋና የስራ አቅጣጫዎች አስቀምጠዋል። አቶ እንጋ እንደገለጹት፣ ስጋት ተኮር ቁጥጥርን ማጠናከር፣ ተቋማት ራሳቸውን እንዲቆጣጠሩ ማስቻል፣ ድንገተኛ ቁጥጥሮችን አጠናክሮ መቀጠል፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን ማስፋት እና የቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር የተቋሙ ዋና የቀጣይ አቅጣጫዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም አዋጅ፣ ደንብና መመሪያዎችን በሚጥሱ እና ለህዝብ ጤና ስጋት በሚያመጡ ተቋማት ላይ ተገቢ እርምጃ መውሰድ የማይታለፍ መሆኑን በንግግራቸው አጽንኦት ሰጥተዋል። ውይይቱ የጋራ መግባባትን በማጠናከር የቁጥጥር ስራዎች በተቀናጀና በውጤታማ መልኩ እንዲፈጽሙ አጋዥ መሆኑ በተሳታፊዎች ተገጿል።
ዜና | Oduu | News
የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ መሆኗን ተከትሎ ለ39ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ ለሚመጡ እንግዶች ማረፊያ በሆኑ በተመረጡ 30 ሆቴሎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ጀምሯል።
ጥር 21, 2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ለ39ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ወደ አገራችን ለሚመጡ እንግዶች የሚያገለግሉ ሆቴሎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እንደመሆኗ በየዓመቱ ከፍተኛ የአፍሪካ እና የዓለም አቀፍ መሪዎችን በመቀበል ረገድ ልዩ ኃላፊነት እንዳለባት ይታወቃል፣ አንደባለስልጣን መስሪያ ቤት ይህ ቁጥጥርም የአገሪቱን መልካም ገጽታ ለማስጠበቅ እንደሚረዳም ተጠቁሟል። ቁጥጥሩ ባለአራትና ባለአምስት ኮከብ ሆቴሎችን ጨምሮ ለጉባኤው የተመረጡ 30 ሆቴሎችን የሚያካትት ሲሆን፣ በተለይም የመኝታ ክፍሎች፣ የምግብ ማብሰያ ቦታዎች እና የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቶች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራበት ይገኛል። በቁጥጥሩ ወቅት የሚገኙ ክፍተቶች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት የማስተካከያ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ባለስልጣኑ ገልጿል። በተለይም ሁሉም በከተማችን ያሉ ሆቴሎች በአገራችን ባህልና ወግ መሰረት ለእንግዶች ቅድሚያ ለመስጠት በሚያስችል አግባብ የተሟላ ዝግጅት እንዲያደርጉ ከወትሮ የተለየ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ እንደሆነም ተገልጿል ። ቁጥጥሩ ጉባኤው እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚቀጥል ሲሆን፣ ዓላማው ሊከሰቱ ከሚችሉ ተላላፊ በሽታዎች እንግዶችን መከላከልና ኢትዮጵያን እንደ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማዕከል ያላትን ሚና ማጠናከር መሆኑ ተገልጿል።
መግቢያ
ስለ_እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
አገልግሎቶች
ተቋማዊ አደረጃጀት
ሚዲያ
ዜናዎች | News
ፎቶግራፎች | Photo Gallery
ቪዲዮዎች | Videos
መግለጫዎች | Press Release
መጽሄቶች | Magazine
ጠቃሚ መረጃዎች
ደንብና መመሪያዎች
ብሮሸር
የደንበኞች የእርካታ ዳሰሳ ገጽ
Online TV
Web APP
ያግኙን
aafdakirkosc1@gmail.com
+251955261273