የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
በጤናው ዘርፍ ሰፍኖ የቆየውን የተበታተነና ጥራት የጎደለውን የአስተዳደርና የቁጥጥር ስርአት ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ አዲስና የተቀናጀ የምግብ፤የመድሀኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ስርአት መዘርጋት በማስፈለጉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክርቤት በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 391/1995 አንቀፅ 14/1/ሀ እና የፌደራል መንግስት የምግብ፤መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 661/2002 አንቀፅ 55 ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን የምግብ የመድሃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳዳርና ቁጥጥር ባለስልጣን በማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 30/2004 እስከ ወረዳ ድረስ ተቋቁሞ በአዋጁ በተሠጠዉ ስልጣን መሰረት ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት የጀመረ መሆኑ ይታወቃል፡፡
የቂርቆስ ቅርንጫፍ ክላስተር 1 ምግብና ጤና ነክ ብቃት ማረጋገጥ የከተማዋን ነዋሪዎች ጤንነት ለመጠበቅ ፣የምግብ እና የጤና ነክ ምርቶች ጥራት፣ደህንነት እና ውጤታማነት ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን የማረጋገጥ ስራ ይሰራል፡፡
ሲ/ር ሳራ ዮሀንስ , የቂርቆስ ቅርንጫፍ ክላስተር 1 የምግብና ጤና ነክ ብቃት ማረጋገጥ ጽ/ቤት ኃላፊ