በጤናው ዘርፍ ሰፍኖ የቆየውን የተበታተነና ጥራት የጎደለውን የአስተዳደርና የቁጥጥር ስርአት ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ አዲስና የተቀናጀ የምግብ፤የመድሀኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ስርአት መዘርጋት በማስፈለጉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክርቤት በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 391/1995 አንቀፅ 14/1/ሀ እና የፌደራል መንግስት የምግብ፤መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 661/2002 አንቀፅ 55 ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን የምግብ የመድሃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳዳርና ቁጥጥር ባለስልጣን በማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 30/2004 እስከ ወረዳ ድረስ ተቋቁሞ በአዋጁ በተሠጠዉ ስልጣን መሰረት ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት የጀመረ መሆኑ ይታወቃል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ፣የመድሃኒት ባለስልጣን አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ደረጃ በደረጃ ለመቅረፍ በተለያየ ጊዜ በተለያየ ደረጃ የተለያዩ ስትራቲጂዎች ተቀርፀው ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡ የአገልግሎት አሠጣጥ ችግር ለመቅረፍ የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ ጥናት (BPR) ክለሳ በማድረግና አደረጃጀቱን በማስፋት እና የሚዛናዊ ስራ አመራርና ውጤት ምዘና (BSC) ተግባራዊ በማድረግ የጤና ፖሊሲ እንዲሁም በቁጥጥር ዘርፍ የሀገሪቱ የማህበራዊ እድገት ከማፋጠንና ኢኮኖሚውን ወደላቀ ደረጃ ከማድረስ አኳያ የህብረተሰቡን ችግሮች በዘላቂነት ለመቅረፍ እስታንዳርዶችን በማውጣት መመሪያዎችን በማዘጋጀት እና መረጃዎችን በማዘመን computerize በማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል፡፡በመሆኑም እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግና የሕብረተሰቡን የእርካታ መጠን ለማሳደግ የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃዎችን በመለየት የዜጎች ቻርተር ተዘጋጅቷል፡፡
የዜጎች ስምምነት ሰነድ ዓላማ
-
የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ፣ ዉጤታማ፣ ተደራሽ በማድረግ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት ፍትሓዊ የመልካም አስተዳደር ስርዓትን ለመዘርጋትና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ፡፡
የጽ/ቤቱ ራዕይ፣ ተልዕኮና ዕሴቶች
የጽ/ቤቱ ራዕይ፣ ተልዕኮና ዕሴቶች ለማወቅ ከፈለጉ ይህን Mission and Vision ይጫኑ
የተገልጋዮች መብት
- መ/ቤቱ ባስቀመጠው የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ መሰረት በክብር የመስተናገድ፣
- በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ቅሬታን የመግለጽና አስተያየት የማቅረብ፣
- ስለመ/ቤቱ አገልግሎት አሰጣጥ አስፈላጊውን እና ማግኘት የሚገባቸውን መረጃ የማግኘት፣
- የመ/ቤቱን የዕቅድ አፈፃፀም ማወቅ ተሳትፎ በማድረግ ማጎልበት፣
- መብትን በአግባቡ የመጠየቅ፣
- በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ቅሬታን የመግለጽና አስተያየት የማቅረብ፣ ፈጣን ምላሽ የማግኘት፣
- ተገልጋዮች አገልግሎቱን በሙሉ ወይም በከፊል ለማግኘት ሲመጡ ማሟላት ያለባቸውን ሁኔታዎች በቅድሚያ የማወቅ መብት አላቻው፡፡
- 9 ሁሉም አገልግሎቱን በእኩልነትና በፍትሐዊነት የማግኘትና የመጠቀም መብት፣ አላቸው።
የተገልጋዮች ግዴታዎች
- አላስፈላጊና ከሥነ-ምግባር ውጪ የሆኑ ባህሪያትን ከማሳየት መቆጠብ፣
- ጥያቄዎችን በግልፅና እንደ አስፈላጊነቱ በህጋዊ ማስረጃዎችና ሰነዶች በማስደገፍ ማቅረብ፣
- አገልግሎቶችን ለማግኘት የተቀመጡትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት፣
- የመሥሪያ ቤቱን ሕግና ሥርዓት የማክበር፣
- ትክክለኛ መረጃ ማቅረብ፤
- በአገልግሎት አሰጣጡ ቅር የተሰኘ የቅሬታ አቀራረብ ስርዓትን በመከተል ቅሬታን ለሚመለከታቸው አካላት በየደረጃው ማቅረብ፣
ተቋሟዊ አደረጃጀት